የሀብተ ሥላሴ ታፈሰን ታሪክ የሚዳስስ መፅሐፍ ተመረቀ

ጥቅምት 28/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢትዮጵያ ቱሪዝም አባት በመባል የሚታወቁትን የሀብተ ሥላሴ ታፈሰን የህይወት ታሪክ የሚዳስስ መፅሐፍ ተመረቀ፡፡

“የ13 ወር ጸጋ” ወይም “13 Months of Sunshine” የሚለውን የቱሪዝም መፈክር በመጠቀም የኢትዮጵያን ቱሪዝም ለዓለም በማስተዋወቅ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ የሚያስቃኘው “THE ARCHITECT OF ETHIOPIAN TOURISM” የተሰኘው መፅሐፍ የታተመው በቱሪዝም ሚኒስቴር አማኝነት መሆኑ ተጠቅሷል።

መፅሐፉ 345 ገጾች እንዳሉትና በታዲ ሊበን በእንግሊዘኛ ቋንቋ መዘጋጀቱ የተገለጸ ሲሆን የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታዎቹ ስለሺ ግርማ እና ሌንሳ መኮንን በተገኙበት በቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ አውደ ርዕይ

የመዝጊያ ስነ – ስርዓት ላይ በይፋ መመረቁን ከቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡