የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በውትድርና ያሰለጠናቸውን ወታደሮች ዛሬ ያስመርቃል

ሐምሌ 17 /2013 (ዋልታ) – የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በመሰረታዊ ውትድርና ያሰለጠናቸውን 2ኛ ዙር ምልምል ወታደሮች ዛሬ እንደሚያስመርቅ ተገለጸ።

ተመራቂዎቹ በቆይታቸው ለውትድርና ሙያ ብቁ የሚያደርጋቸውን የመሰረታዊ ውትድርና ስልጠና አመርቂ በሆነ መልኩ ወስደው አጠናቀዋል ተብሏል።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ጀኔራል መኮንኖች፣ የትምህርት ቤቱ አዛዥ ኮ/ል አዲሱ ተርፋሳ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።