የህዳሴ ግድብ ትስስር ምስረታ ተካሄደ

ሰኔ 12/2013 (ዋልታ) – የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ትስስር ምስረታ ዛሬ ተካሂዷል፡፡

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ብሄራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ከኢትዮ ሴፍቲ የትምህርት አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ጋር በመተባበር “ስለ አባይ ዝም አልልም” በሚል ሀሳብ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

ውይይቱ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ከኢትዮ ሴፍቲ የትምህርት አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ጋር ያዘጋጁት ነው፡፡

የውይይቱ አላማ የታላቁ ህዳሴ ግድብን ለማጨናገፍ በሀገር ውስጥና በውጪ ሀይሎች የሚሰራውን ሴራ በማጨናገፍ ህጋዊ ምላሽ መስጠትና የጂኦ-ፓለቲካዊ ውጥረቱን በማርገብ የመፍትሄ ሀሳቦችን ማንፀባረቅ ነው ተብሏል።

በመድረኩ ላይ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ  የህዝቡ ተሳትፎ ምን ይመስላል በሚለው ሀሳብ ላይ ገለፃ እየተደረገም ነው፡፡

ጉባኤው ኢትዮጵያዊያን በግድቡ ጉዳይ በአንድነት እንዲቆሙ ይሰራል ተብሏል፡፡

በጉባኤው ምስረታ ላይ  የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ድክተር ስለሺ በቀለ ተገኝተዋል።

(በሱራፌል መንግስቴ)