የሶማሌ ክልልና የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የምእራብ ጎዴይ የመስኖ ልማት ፕሮጀክትን ጎበኙ

ኅዳር 12/2014(ዋልታ) የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ኡስማን ፋራህ እና የመስኖና ቆላማ አከባቢዎች ልማት ሚኒስትር ኢ/ር አይሻ መሐመድ፣ የግብርና ሚኒስትር አቶ ዑመር ሁሴን፣ የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ አመራር ልዑካን በምዕራብ ጎዴይ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት ስራ ሂደት የመስክ ምልከታ ጉብኝት አደርገዋል።

ጉብኝቱ የሸበሌ ወንዝ መስኖ ፕሮጀክትን ሂደት፣ በአከባቢው ላይ የተሰራው የግብርና ሥራዎችና አጠቃላይ የፕሮጀክቱ ሁኔታ ለመመልከት ያለመ ነው ተብሏል። ፕሮጀክቱ የሚያመርቷቸው ምርቶችና አሁናዊ ገፅታዎችም ተጎብኝተዋል።

በምዕራብ ጎዴይ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት ስራ ጉብኝት ያደረጉት የፌዴራል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ሚኒስቴሮችና የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፕሮጀክቱን ለማጠናከር በጋራ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

ባለፈው ሳምንት በርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ዑመር የሚመራ የክልሉ ካቢኔ አባላት ፕሮጀክቱን መጎበኘታቸውን ይታወሳል።

የክልሉ መንግሥት በክልሉ የሚገኙ ተፋሰሶችን ተገቢውን ትኩረት በመስጠት በአሁኑ ጊዜ በርካታ የግብርና ምርቶች በመመረት ላይ እንደሚገኙ ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።