የብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ

ግንቦት 7/2014 (ዋልታ) የብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ፡፡
ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ለአንድ ቀን በሚያካሂደው ስብሰባ የብልፅግና ፓርቲ 1ኛ ጉባዔ ባስቀመጣቸው አቅጣጫዎችና ውሳኔዎች ላይ ከሊጉ አባላት ጋር በየደረጃው የተደረገውን ውይይት የአፈፃፀም ሁኔታ እንደሚገመግም ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም “ምግቤን ከጓሮዬ፤ ጤናዬን ከምግቤ” በሚል መሪ ቃል በመላ ሀገሪቱ የተጀመረው የከተማ ግብርና ንቅናቄ የአፈፃፀም ደረጃ በየክልሎችና በሁለቱ ከተሞች የሊጉ አመራሮች ሪፖርት ቀርቦለት እንደሚወያይ ከብልጽግና ፓርቲ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡