የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የንግዱን ዘርፍ የሚደግፍ አካዳሚ ይፋ አደረገ

ሚያዝያ 17/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የግሉን ዘርፍ ለመደገፍና የአቅም ግንባታ ስራዎችን በቢዝነስ መስኮች ተደራሽ ለማድረግ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የንግድ አመራር አካዳሚን ይፋ አድርጓል፡፡

ለንግድ አመራር አካዳሚው ስልጠናውን ለማካሄድ የሚያግዝ የ230 ሺሕ ዩሮ ድጋፍ መደረጉም ተገልጿል፡፡

አካዳሚው የሴቶችን የአመራር ብቃትን ለማሳደግ፣ አካል ጉዳተኞችን ተሳታፊ የሚያደርግ እንዲሁም ዘመኑን የዋጁ የአይሲቲ ቴክኖሎጂዎችን መሰረት ያደረጉ ስልጠናዎች ማዘጋጀቱን አመላክቷል፡፡

የንግድ አመራር አካዳሚ ስልጠናውን ማግኘት የሚፈልጉ የንግዱ ማህበረሰብ ባሉበት በሁሉም የአገሪቷ አካባቢዎች ማግኘት እንደሚችሉ ጠቁሟል፡፡

ምክር ቤቱ የግሉ ዘርፍ በኢኮኖሚው አበረታች እንቅስቃሴ እንዲኖረው የምርምር፣ የንግድና ኢንቨስትመንት ማስፋፊያ እንዲሁም የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ሲሰጥ መቆየቱ ነው የተገለጸው፡፡

ከዚህ ቀደም በነበሩት የንግድ መስክ ስልጠናዎች ከ150 ሺሕ በላይ ዜጎች ተሳታፊ መሆናቸውም በመድረኩ ተገልጿል፡፡

በሳራ ስዩም

S