የኢትዮጵያ በፈተናዎች ሁሉ የተሻገረ ያለመበገር ፅናት የምጣኔ ሀብት መረጋጋትን እና ምርታማነትን ባስቀደሙት በመዋቅራዊ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ስራዎቿ ማሳያነት ይገለጣል – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ጠቅላ ሚኒስትር ዐቢ አህመድ

ሚያዚያ 21/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢትዮጵያ በፈተናዎች ሁሉ የተሻገረ ያለመበገር ፅናት የምጣኔ ሀብት መረጋጋትን እና ምርታማነትን ባስቀደሙት በመዋቅራዊ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ስራዎቿ ማሳያነት ይገለጣል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

በብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን በሚመራው ስራ ምክክር እና እርቅ የሰላም ፍላጎታችን እና ተምኔታችን ማጠንጠኛ ናቸው ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

ትምህርትን ተደራሽ በማድረግ ብሎም ወጣቶችን በማብቃት ኢትዮጵያ ሁለት ሚሊዮን አዳዲስ ስራዎችን ለመፍጠር አልማለች ነው ያሉት።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረንጓዴ ዓሻራ በመሰሉ ንቅናቄዎች ኃይል ለሁሉም ማዳረስ፣ የዲጂታል ሽግግር እና የተፈጥሮ ከባቢን የመንከባከብ ተግባራትን ለመከወንም ትኩረት እንደምትሰጥ ገልጸዋል።

የዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር ለአሕጉሩ ድጋፉን እንዲያጠናክር ኢትዮጵያ ጥሪ ታደርጋለች ብለዋል።