የኢትዮጵያ፣ ሩስያ እና ጂቡቲ የቢዝነስ ፎረም ተካሄደ

ጥር 17/2014 (ዋልታ) የአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ትብብር አስተባባሪ ኮሚቴ ከሩስያ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ጋር በጋራ ያዘጋጁት የኢትዮጵያ፣ ሩስያ እና ጂቡቲ የበይነመረብ የቢዝነስ ፎረም ተካሂዷል።

በመድረኩ የኢትዮጵያ እና ጂቡቲ የሩሲያ አምባሳደሮች፣ በሩስያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ፣ የየሀገራቱ የንግድ ምክር ቤት ተወካዮች እንዲሁም የሚመለከታቸው የዘርፉ ተቋማት ተሳትፈዋል።
መድረኩ በአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ትብብር አስተባባሪ ኮሚቴ ሊቀ-መንበር ኢጎር ሞሮዞብ ሰብሳቢነት ተመርቷል።
በኢትዮጵያ በኩል ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ ከቡናና ሻይ ላኪዎች ማኅበር እንዲሁም ከኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ተወካዮች ተሳትፈዋል።
ፎረሙ ለአነስተኛና መካከለኛ የሩስያ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ እና ጂቡቲ ያለውን የኢንቨስትመንት እድሎች የማስተዋወቅ እና በሀገራቱ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ የንግድ ልውውጥ እና የኢኮኖሚ ግንኙቱን የበለጠ ለማሳደግ ያለመ ነው።
እ.አ.አ በቀጣዩ የካቲት ወር የአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ትብብር አስተባባሪ ኮሚቴ በኢትዮጵያ እና ጂቡቲን ለሚልካቸው የቢዝነስ ልዑካን ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር መሆኑም ተጠቅሷል።
በተያያዘም የአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ትብብር አስተባባሪ ኮሚቴ የሩስያ የቢዝነስ ድጋፍ ሰጪ ማዕከል በሁለቱ ሀገራት በቅርቡ የማቋቋም እቅድ አንዳለው መገለጹን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።