መስከረም 6/2014 (ዋልታ) የኦሮሚያ ክልል ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ከ114 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ከ3 ሺሕ 600 በላይ በሬዎች፣ ፍየሎች እና በጎች ለሁለተኛ ጊዜ ድጋፍ አደረገ።
ክልሉ የአሸባሪ ሕወሓት ቡድን ሀገርን ለማፍረስ የጀመረውን የተደራጀ ዘመቻ ለመመከት ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመቆም 1 ሺሕ 411 በሬዎች፣ 1 ሺሕ 85 ፍየሎች እና 3 ሺሕ 656 በጎች ድጋፍ ማድረጉ ተመላክቷል።
ድጋፉ ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን ክልሉ እስካሁን በድምሩ ከ242 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ማድረጉን የኦሮሚያ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ መስከረም ደበበ ገልጸዋል።
የክልሉ ህዝብ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚያደርገው ድጋፍ ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኃላፊዋ ተናግረዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የሀገር መከላከያ ሰራዊት የግዥ ዳይሬክቶሬት ዋና ዳይሬክተር ሌተናል ጀነራል አለምሰገድ ወንደወሰን ድጋፍ ያለው ሰራዊት ሁሌም አሸናፊ ስለሆነ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
በቡላ ነዲ
ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW