የክልሎች የሰላም እና የጋራ ልማት እቅድ ስምምነት አስተማማኝ የሀገራዊ እድገት እመርታ አስተዋጽኦው ከፍተኛ ነው- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

 

በክልሎች ውስጣዊ እና አስተዳደራዊ ወሰን አካባቢዎች የሰላም እና የጋራ ልማት እቅድ ስምምነቶችን ማከናወን አስተማማኝ የሀገራዊ እድገት እመርታ ላይ የሚያመጣው ተጽዕኖ እጅግ ከፍተኛ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት የኦሮሚያ እና ሱማሌ ክልል አመራሮች ላሳዩት ምሳሌያዊ ተግባር ላቅ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል።

ሁሉንም የሀገራችንን ክፍል በሰላምና አብሯዊ ልማት አሰናስለን ብልጽግናችንን እውን እናደርጋለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።