የወራቤ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዙር ተማሪዎቹን አስመረቀ

በ2010 ዓም የተመሰረተው የወራቤ ዩኒቨርሲቲ 1ሺህ 77 ተማሪዎቹን ዛሬ አስመርቋል።

ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱን በመጠበቅ እና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን በመከላከል 612 ሴት እንዲሁም 465 ወንድ ተመራቂዎቹን ያስመረቀው የወራቤ ዩኒቨርሲቲ በዚህ አመት የሁለተኛ ድግሪ ትምህርት እንደሚጀምርም ተገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው በአራት ኮሌጆች፣ 14 የትምህርት ክፍሎች፣ 1ሺህ 77 ተማሪዎችን የሚያስተምር ሲሆን በመደበኛ የትምህርት መርሀ ግብር በ49 የትምህርት መስኮች 3ሺህ 347 ተማሪዎችን ተቀብሎ ያስተምራል።

የመጀመሪያ ዙር የምረቃ ስነስርአቱ ላይ የቀድሞው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ፣ የሰላም ሚንስትር ሙፈርያት ካሚል፣ በሚንስትር ዴኤታ ማዕረግ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ አቶ ጫላ ለሚ፣ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳደር አቶ አሊ ከድር፣ የዩኒቨርሲቲው ም/ቦርድ ሰብሳቢ እንዲሁም ከዞን እና ከወረዳ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተውበታል።

(በቁምነገር አህመድ)