የካቲት 17፣ 2013 (ዋልታ) – 125ኛውን የአድዋ ድል በዓል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለማክበር የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሂሩት ካሳው አሶሳ ከተማ ገቡ።
በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሌ ሀሰን የተመራው የክልሉ ከፍተኛ አመራርም ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በዓሉም ከዛሬ ጀምሮ በፓናል ውይይት እና ታሪካዊ ቦታዎችን በመጎብኘት እንደሚካሄድ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡