ጥቅምት 5/2016 (አዲስ ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኬ ያንግ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸው ወቅትም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የምጣኔ ኃብት ትብብር ግንኙነት ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመንግስታቸውን ባለብዙ ዘርፍ የእድገት አላማ ብሎም የተገኙ ድሎችን በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መረጃ እንዳመላከተው በተጨማሪም ከቻይና ጋር የንግድ ግንኙነቶችን ማስፋፋት አስፈላጊ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኬ ያንግ በበኩላቸው ሁለቱ ሀገራት በማደግ እና በመጎምራት ላይ ያለ ኢኮኖሚ ባለቤቶች እንደመሆናቸው በጋራ የማደጊያ መንገዶችን ሊቀይሱ እንደሚችሉ አውስተዋል።
ከውይይታቸው በኋላም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኬ ያንግ በሁለቱ ሀገራት መካከል በተለያዩ መስኮች 12 ያህል የትብብር ስምምነቶች እና ሁለት የፍላጎት ሰነዶች በተፈረሙበት ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተዋል።