ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ይፋ ተደረገ

ፍሬህይወት ታምሩ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ

የካቲት 11/2013 (ዋልታ) – ኢትዮ ቴሌኮም አዲሱን ”4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ” የተባለ ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት በደቡብ ምስራቅ ሪጅን ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ይፋ ተደርጓል፡፡

አገልግሎቱ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎትን በላቀ ፍጥነት መጠቀም የሚያስችል ነው ተብሏል::

ከአንድ አመት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ ተደርጎ የነበረ ሲሆን በክልል ደረጃ የዛሬው የመጀመሪያ ነው ተብሏል።

ከአዲሰ አበባ ከተማ ውጪ ለመጀመሪያ ጊዜ በደቡብ ምስራቅ ሪጅን ከተሞች በአዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ዱከም ፣ሞጆ፣  ገላንና አዋሽ መልካሳ የተጀመረ ነው።

ይህ ኤል.ቲ.ኢ ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት ቀደም ሲል በአካባቢው ከነበሩት የ3ጂ የኢንተርኔት አገልግሎት በጣም ፈጣን መሆኑም ተጠቁሟል።

ይህም ደንበኞች በላቀ ፍጥነት የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎተ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ነው የተባለው።

በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ የነበረውን የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት በማስፋት በ103 ከተሞች ተደራሽ ለማድረግ መታሰቡን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገልፀዋል።

የማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ሲሆን አገልግሎቱ ተግባራዊ የሚደረግባቸው ከተማ አመራሮችና ሌሎች የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል ሲል፡፡

(በሃኒ አበበ)