ሚያዝያ 05/2013 (ዋልታ) – ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የዓለም ዓቀፉ የትምህርት ስርዓት የወደፊት ሁኔታ ላይ ለመምከርና ለማቀድ ከተቋቋመው ኮሚሽን ጋር ተወያይተዋል፡፡
ከመላው ዓለም የተውጣጡ ምሁራንንና ባለሙያዎችን ያቀፈው ኮሚሽኑ ለወደፊት ዘመናዊ እና ሁሉን አቀፍ ትምህርት ምን መምሰል እንዳለበት ለፖሊሲ አውጭዎች፣ ለመምህራንና ለተማሪዎች መመሪያ ሆኖ የሚያገለግል ሪፖርት እያዘጋጀ ነው ተብሏል፡፡
ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ እንዳመላከተው ኮሚሽኑ እስካሁን የተሠራውን ሥራና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተገኙ አስተያየቶች ላይ ተወያይተዋል፡፡