ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ በሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ካጋሜ በሚመራው የ“ስማርት አፍሪካ” የቦርድ ስብሰባ ላይ ተሳተፉ

ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ በሚመራው የ‘ስማርት አፍሪካ’ ቨርቹዋል የቦርድ ስብሰባ ላይ ተሳትፈዋል፡፡
‘ስማርት አፍሪካ’ በአህጉሪቱ ቀጣይነት ያለው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት እንዲፋጠን በአፍሪካ መሪዎች ተነሳሽነት የተጀመረ ፣ የአፍሪካን ብሮድባንድ ተደራሽነት እና የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዕድገትን ለማሳለጥ የተነደፈ ዕቅድ ነው፡፡
ፕሬዝዳንቷ በኢትዮጵያ የፀደቀውን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ እና የተወሰዱ እርምጃዎችን በተመለከተ ለተሰብሳቢዎች ገለፃ ማድረጋቸውን ከፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡