ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ንፁሃን ላይ የተፈፀመውን ግድያ በፅኑ አወገዙ

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

ሰኔ 15/2014 (ዋልታ) ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ባለፉት ቀናት በበርካታ ንፁሃን ላይ የተፈፀመውን ግድያ በፅኑ እንደሚያወግዙ ገለጹ።

ፕሬዝዳንቷ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለን (ዶ/ር) ስለ አገራችን ሰብአዊ መብት ሁኔታ ማነጋገራቸውን ጠቁመዋል።

በተለይም ባለፉት ቀናት ሴቶች እና ሕፃናትን ጨምሮ በበርካታ ንፁሃን ዜጎች ላይ ስለተፈፀመው አሰቃቂ ግድያ እንደተወያዩ ነው ያስታወቁት።

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ይህን አሰቃቂ ድርጊት በፅኑ እንደሚያወግዙም በቲውተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት ገልጸዋል።

“በየትም ቦታ የዜጎች ሕይወት ውድነቱ እና ክብሩ መሸርሸር የለበትም” ያሉት ፕሬዝዳንቷ “ሞትን ከተለማመድነው ከግድያ በኋላ ከማውገዝ እና የሀዘን መግለጫ ከማውጣት አዙሪት አናልፍም፤ ከዚያ በላይ መሔድ ይኖርብናል” ሲሉም አስገንዝበዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW