የአፍሪካ ቀንድ ስጋት ስለሆነው አሸባሪው ሕወሓት ለእንግሊዝ ማብራሪያ

መስከረም 15/2014 (ዋልታ) በእንግሊዝ የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ እንግሊዝና የተቀረው ዓለም ዐቀፍ ማኅበረሰብ የአሸባሪውን ሕወሓት ድርጊት እንዲያወግዙና የሰብኣዊ ድጋፍን እንዲያሳድጉ ጠየቁ።

አምባሳደሩ ጥሪውን ያቀረቡት ከእንግሊዝ የሕዝብ እንደራሴ ላውረንስ ኢሮበርትሰን ጋር በተወያዩበት ወቅት እንደሆነ በቲውተር ገፃቸው ጽፈዋል።

አምባሳደሩ በውይይታቸው በኢትዮጵያ የሰብኣዊ አቅርቦትን ማሳደግ በሚቻልበት ስልት ላይ ስለመምከራቸው ነው ያስታወቁት።

የእንግሊዝ የሕዝብ እንደራሴዎች እና ዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ የአሸባሪውን ሕወሓት ሰፊ ወረራና ጥቃት ሊያወግዝ እንደሚገባ አፅንኦት መስጠታቸውንም አክለዋል።

አምባሳደር ተፈሪ የሽብር ቡድኑ ከኢትዮጵያ ባሻገር የአፍሪካ ቀንድ ያለመረጋጋት (የፀጥታ) ቀጥተኛ ስጋት እንደሆነም አብራርተዋል።