ስዊድን በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል 6 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ አደረገች

የስዊድን መንግስት በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል 6 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

ድጋፉ በትግራይ ክልል በተካሄደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ለተጎዱ ዜጎች የሚሰጥ ሲሆን በዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማህበር፣ በዓለም የምግብ ፕሮግራም እና በዓለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም አማካኝነት ለተጎጂዎች የሚደርስ መሆኑን ከስዊድን ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡