የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 45 ያህል ፓርቲዎች ምልክቶቻቸውን ያስገቡ መሆኑን ገልጾ የሚከተሉት ፓርቲዎች የመረጧቸው ምልክቶች በተለያዩ ምክንያቶች እንዲቀይሩ ጥሪ አቅርቧል።
- የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ – የመረጠው ምልክት ከዚህ በፊት በነበረው ምርጫ ሌላ ፓርቲ ሲጠቀምበት የነበረ በመሆኑ እና ፓርቲው የቀድሞ ምልክቱን ለመጠቀም በመጠየቁ
- የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ- የመረጠው ምልክት ከዚህ በፊት በነበረው ምርጫ ሌላ ፓርቲ ሲጠቀምበት የነበረ በመሆኑ እና ፓርቲው የቀድሞ ምልክቱን ለመጠቀም በመጠየቁ
- የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ – የመረጠው ምልክት ከዚህ በፊት በነበረው ምርጫ ሌላ ፓርቲ ሲጠቀምበት የነበረ በመሆኑ እና ፓርቲው የቀድሞ ምልክቱን ለመጠቀም በመጠየቁ
- የምእራብ ሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ – ከሌላ ፓርቲ ምልክት ጋር ምልክቱ የተቀራረበ በሆኑ
- የአርጎባ ብሔረሰብ ዴሞክራሲያቂ ንቅናቄ- ከሌላ ፓርቲ ምልክት ጋር ምልክቱ የተቀራረበ በመሆኑ
- የኦሮሞ ነጻነት ግንባር – ህጋዊ ሃላፊነት በተሰጠው አካል ምልክታቸውን እንዲመርጡ የተጠየቁ (በዚህም መሰረት የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ የምርጫ ምልክት አስገብተዋል።)
በተጨማሪም የምርጫ ምልክቶቻቸውን ያላስገቡ ወይም መቀየር የሚፈልጉ ፓርቲዎች እስከ ጥር 23 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ እንዲያጠናቅቁ ቦርዱ አሳስቧል፡፡