ቦርዱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመራጮች ምዝገባ ጊዜን አራዘመ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ግንቦት 11/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመራጮች ምዝገባ ጊዜን አራዝሟል፡፡

ቦርዱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመራጮች ምዝገባ በኢንተርኔት እንደሚከናወን ማሳወቁ እንዲሁም ይህንን ተከትሎ ምዝገባ ሲከናወን እንደነበር ይታወቃል።

በየምርጫ ጣቢያዎቹ የሚደገረው መራጮች ምዝገባ ቢጠናቀቅም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ተጨማሪ የምዝገባ ጊዜ መሰጠት እንዳለበት ቦርዱ ወስኗል።

በዚህም መሰረት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች እስከ ግንቦት 17 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ https://www.ovrs.gov.et በሚገኘው የመመዝገቢያ ሊንክ በመጠቀም መመዝገብ እንደሚቻል አሳስቧል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት www.nebe.org.et የምዝገባ ሊንክ ድረ-ገጽ መመዝገብ እንደሚችሉም ከምርጫ ቦርድ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሚዲያዎች እንዲሁም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም ይህንን የኦንላይን ምዝገባ በማስታወስ ምዝገባቸውን እንዲያከናውኑ እንዲያደርጉ ቦርዱ ጥሪ አቅርቧል።