ሀገርን ማገልገል ዕድል፣ ተልዕኮን መፈጸም ደግሞ ድል ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ታኅሣሥ 25/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሀገርን ማገልገል ዕድል፣ ተልዕኮን መፈጸም ደግሞ ድል ነው ሲሉ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው የአገልግሎት ዘመናቸውን ያጠናቀቁ አምባሳደሮቻችንን ኢትዮጵያ ታመሰግናቸዋለች፤ እኔም በዓለም መድረክ ላይ ሳይቆጠቡ ላሳዩት ውክልና ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያን በመወከል በተለያዩ አገራት በአምባሳደርነት አገልግለው የስራ ዘመን ቆይታቸውን አጠናቀው ወደ አገራቸው ለተመለሱ አምባሳደሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምስጋና እና እውቅና መስጠቱ ይታወሳል፡፡