መስራች ጉባኤው የክልሉ የብሄረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ እና ምክትል አፈ ጉባኤ መረጠ

ታኅሣሥ 25/2015 (ዋልታ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብሔረሰቦች ምክር ቤት ቴፒ ከተማ ባካሄደው የመስራች ጉባኤ መቱ አኩን የክልሉ መንግስት የብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አድርጎ መርጧል፡፡

የዋና አፈ ጉባኤ መቱ አኩ ሹመት በምክር ቤት አባላት በሙሉ ድምጽ ጸድቋል፡፡ ዋና አፈ ጉባኤውም በምክር ቤቱ አባላት ፊት ቀርበው ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።

ምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው እንዲመሩ መሰለ ከበደ በምክር ቤቱ አባላት ሙሉ ድምጽ የተመረጡ ሲሆን  በምክር ቤቱ አባላት ፊት ቀርበው ቃለ መሀላ መፈጸማቸውን የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ መረጃ ያመለክታል፡፡