ሀገር አቀፍ የኮቪድ- 19 ላይ የተሰሩ ጥናታዊ የምርምር ስራዎች ጉባኤ ማጠቃለያ ተካሄደ

ሰኔ 5/2013(ዋልታ) – ኮቪድ 19 ሊያመጣ ይችል የነበረውን ከፍተኛ ጉዳት በመቀነስ ረገጽ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚናቸው ከፍተኛ ነው ሲሉ ም/ ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡

ም/ ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህንን ያሉት ለሁለት ቀን ሲካሄድ የነበረዉ ሀገር አቀፍ የኮቪድ – 19 ላይ የተሰሩ ጥናታዊ የምርምር ስራዎች ማጠቃለያ ጉባኤ ላይ ነው፡፡

ካቪድ 19ን ለመከለከል ከዘመቻ በዘለለ በሲስተም ውስጥ አካቶ መስራት ያስፈልጋልም ብለዋል።

ም/ ጠቅላይ ሚንስትሩ ለዚህም ጥናታዊና የምርምር ስራዎችን መነሻ በማድረግ ሀገራዊ አቅምን መፈጠር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርና የጤና ሚኒስቴር በአዘጋጁት ኮንፍራንስ ላይ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በኮቪድ ዙሪያ ይዘዋቸው የመጡትን የምርምር ስራዎች አቅርቧል ።

በማጠቃላያ መድረኩ የተገኙት ም/ ጠቅላይ ሚኒስተርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ቦቪድ 19ን በመከላከል ረገድ በዘርፉ ብዙ ስራዎች በመሠራታቸው ወረርሽኙ ሊያደርስ የሚቻለውን ጉዳት መቀነስ ቢቻልም የመርመር አቅም ባያድግ ጉዳቱ ከዚህም በላይ ሊሆን ይቻላል ብለዋለ፡፡

የጤና ማኒስተር ዶ/ር ሊያ ታደስ ዳግሞ ትኩረት ለኮቪድ 19 በሚል የተጀመረው ንቅናቄ ግቡን እንደመታ እና ከዚህ ቀደም ከነበረው የኮቪድ ምላሽ አሰጣጥ በተሻለ በኮቪድ 19 ላይ የተሰሩ ጥናቶችን ግብኣት ማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ብለዋል ።

የምርምር ስራዎች እንዲጠነከሩ በቅንጅት መሰረተ አስፈላጊ ነው ያሉት ጤና ሚኒስትሯ በዚህም ጤና ሚኒስቴርም 50 ማለየን ብር ወጪ አድርጎ የጥናትና የምርምር ስራዎችን እየደገፈ ነው ብለዋል፡፡

በመስከረም ቸርነት