ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት የምክክር ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሀደ ነው

ሚያዚያ 7/2016 (አዲስ ዋልታ) ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት የምክክር ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በጉባዔው የሃይማኖት መሪዎች፣ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ ሚንስትሮች ፣ አምባሳደሮች፣የአፍሪካና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ተገኝተዋል።

ኮንፈረንሱ በአፍሪካ ውስጥ የሃይማኖቶች የጋራ ተግባርን ለማስከበር እና ለማበረታታት፣ ሰላምን፣ ሰብአዊ ክብርን፣ ልማትን እና አካባቢን መጠበቅ እና የጥላቻ ንግግርን ፣ ጥቃትን እና የውጭ ዜጋ ጥላቻን መከላከል በሚል መሪቃል እየተካሄደ ነው ።

በአህጉርና ዓለም አቀፍ ደረጃ ሠላምና ልማትን ማረጋገጥ፣ ሰብዓዊ ክብርን መጠበቅ፣አካባቢን መጠበቅ፣ የጥላቻ ንግግርንና መጤ ጠልነትን በጋራ መከላከል የሚያስችል ምክክር ማድረግ የጉባኤው ዋና ዓላማ መሆኑም ተገልጿል።

ጉባዔው የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ የበላይ ጠባቂነት የተዘጋጀ ሲሆን ዛሬ እና ነገ ለሁለት ቀናት ይካሄዳል።

በሰማኸኝ ንጋቱ