ማሽነሪ አምራች ኢንዱስትሪዎች ሀገራዊ እድሎችና ተግዳሮቶችን የተመለከተ ውይይት እየተካሄደ ነው

ሚያዚያ 7/2016 (አዲስ ዋልታ) ማሽነሪ አምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ ያሉ ሀገራዊ እድሎችና ተግዳሮቶችን የተመለከተ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

መድረኩ የተዘጋጀው በኢንዱስትሪ ሚኒስትርና በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አማካኝነት ነው።

ዘርፋ በኢትዮጵያ ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝና አለማቀፋዊ ተሞክሮዎች ምን እንደሚመስሉ በመደረኩ ተነስቷል።

በተለይ ከዚህ ቀደም እምብዛም ትኩረት ያልተሠጠው የማሽነሪ አምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅምን ከማሳደግ አኳያ መድረኩ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተጠቁሟል።

ኢትዮጵያ ማሽኖችን ከውጭ የምታስገባ ሲሆን በዚህም በየአመቱ በርካታ የውጭ ምንዛሬ እንደምታጣ ነው የተገለጸው።

ይህንን ለማስቀረትና የሀገር ውስጥ አምራቾችን ለማበረታታት ከቅርብ አመታት ወዲህ ለዘርፉ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ነው ተብሏል።

የጥሬ እቃ ከቅርቦት ችግር፣ የፋይናንስ አቅርቦት አጥረት፣ ቦታ አለማግኛት፣የክህሎት ክፍተት እና መሰል ችግሮች በተግዳሮትነት ተነስቷል።

እነዚህን ችግሮች ለመፍታት በቀጣይ የሚሠሩ ስራዎችን በተመለከተም በመድረኩ ላይ ተነስቷል።

በቤዛዊት አበበ