ህወሓት ከአማራና አፋር ክልል ለቆ እንዲወጣ የአሜሪካ ዓለም አቀፋ ተራዕዶ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዳግም ጥሪ አስተላለፉ

ነሀሴ 17/2013 (ዋልታ) – ህወሓት በአማራ እና አፋር ክልል እየፈፀመ ያለውን ጥቃት እንዲያቆምና ከሁለቱ ክልሎች ለቆ እንዲወጣ የአሜሪካ ዓለም አቀፋ ተራዕዶ ድርጅት (USAID) ዋና ዳይሬክተር ሳማንታ ፓወር በቲዊተር ገጿ ጥሪ አስተላለፈች።

ዋና ዳይሬክተሯ ጥሪውን ሲያስተላልፉ ያሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው።

ህወሓት እየፈፀመ ያለው ጥቃት ግጭቱን ከማባባስ የዘለለ ለኢትዮጵያዊያን መፍትሄ እንደሌለውም የገለፀችው  ሳማንታ ፓወር

ቡድኑ እያደረሰ ያለውን ጥቃት በማቆም ለውይይት መቀመጥ ይኖርበታል  ስትልም መልዕክቷን በቲዊተር ገጷ አስፍራለች።

የተራዕዶ ድርጅቱ በአፋርና አማራ ክልል በፈጸመው ጥቃት ለተጎዱ ከ136ሺህ በላይ ዜጎች ድርጅታቸው ምግብ ማቅረቡንም ገልጻለች።

ህወሃት በሁለቱ ክልሎች ብቻ በፈፀመው ጥቃት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን ዋና ዳይሬክተሯ በትዊተር ገጿ ላይ ባሰፈረችው ጽሁፍ ገልጻለች።