ህገወጥ የጦር መሳሪያዎችን ሲያዘዋውር የተያዘ ተጠርጣሪ

መስከረም 15/2014 (ዋልታ) የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመቀናጀት ባደረጉት  ክትትል ህገወጥ የጦር መሳሪያዎች ተያዙ።

በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 የሚኖር እሸቴ ፀጋዉ የተባለ ተጠርጣሪ  ከጎንደር ከተማ  ወደ ባህር ዳር ከተማ በኮድ 2 አማ 24492 ዳማስ መኪና ሻግ በማሰራት በርካታ ጥይቶችን ደብቆ ለማሳለፍ ሲሞክር የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ባደረጉት የተቀናጀ ክትትል ማዕከላዊ ጎንደር ኢንፍራንዝ ከተማ ላይ በቁጥጥር ስር ዉሏል፡፡

ተጠርጣሪዉ 3,375 የክላሽንኮቭ ጥይቶችን እና 783 የብሬን ጥይቶችን ደብቆ ሊያሳልፍ ሲሞክር  እጅ ከፍንጅ መያዙን ተገልጿል፡፡

በግለሰቡ መኖሪያ ቤት ዉስጥ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻም ተጨማሪ አንድ ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ከ2100 ጥይቶቻ ጋር ተይዟል፡፡