የፕሬዝዳንቷ ጉብኝት በደሴ

መስከረም 15/2014 (ዋልታ) የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በአሸባሪው ትሕነግ ከሰሜን ወሎ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደሴ ከተማ የተጠለሉ ወገኖችን እና በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን የጸጥታ አባላት ጎበኙ።

ፕሬዝዳንቷ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመርዳት የሚደረገው ርብርብ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደቀያቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ይሰራል ብለዋል።

ለተፈናቀሉ ወገኖች መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይ ደግሞ የደሴ ከተማ ነዋሪዎች የመጀመሪያ ደራሽ በመሆን ላደረጉት መልካም ተግባር ምስጋና አቅርበዋል።

የደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ሠራተኞች በጦርነቱ ለተጎዱ የጸጥታ አባላት እየሰጡት ለሚገኙት አገልግሎትም አመስግነዋል፡፡

በደሴ መጠለያ ጣቢያዎች ያሉ ተፈናቃይ ወገኖች ቁጥር ከ350 ሺሕ በላይ ደርሷል፡፡