ለሽብር አላማ በ2 ተሽከርካሪዎች ተጭኖ ሲጓጓዝ የነበረ የጦር መሣሪያ ተያዘ

ሐምሌ 19/2013 (ዋልታ) – ለሽብር አላማ በ2 ተሽከርካሪዎች ተጭኖ ሲጓጓዝ የነበረ የጦር መሣሪያ መያዙን የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት እና ከህብረተሰቡ ጋር ባደረገው ክትትል ለተለያዩ የሽብር አላማዎች ማሳኪያ በ2 ተሽከርካሪዎች ተጭኖ ሲጓጓዝ የነበረውን 35 ክላሽንኮቭ መሣሪያዎች ከካርታዎች ጋር እንዲሁም ከ 3 ተጠርጣሪዎች ጋር ነው በቁጥጥር ስር ለማዋል የቻለው፡፡
ሲጓጓዝ የነበረውን የጦር መሳሪያ ከነተጠርጣሪዎቹ ጋር በቁጥጥር ስር የዋሉት ደቡብ ክልል ቡታጅራ ከተማ ሲደርስ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
አንዱ ተጠርጣሪ ለጊዜው በመሠወሩ ክትትል እየተደረገ እንደሆነም የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ ያመለክታል፡፡