የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚያደርገውን ዘመቻ እንሚደግፉ የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ



ሐምሌ 19/2013 (ዋልታ) –
የሀገር መከላከያ ሰራዊት የህወሓት ጁንታ ቡድንን ለመደምሰስ የሚያደርገውን ዘመቻ እንሚደግፉ ዋልታ ያነጋገራቸው የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
ፅንፈኛው ቡድን ፈፅሞ የኢትዮጵያዊነት ስሜት የሌለው እንደሆነ የሚገልፁት ነዋሪዎቹ ጁንታውን ለማጥፋት በሚደረገው ዘመቻ ከሀገር መከላከያ ጎን እንደሚቆሙ ተናግረዋል።
ሀገር እንድትጠፋ የሚፈልግን ቡድን ማጥፋት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ሃላፊነት ሊሆን እንደሚገባም ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል።
ጁንታው ወደ ሰላም እንዲመጣ በርካታ እድል ቢሰጠውም እድሉን አለመጠቀሙ በተግባር ሽብርተኛ መሆኑን አመላካች ነውም ብለዋል።
ፅንፈኛው ቡድንን በመደምሰሱ ሂደት እስከ ግንባር ለመዝመት ዝግጁ መሆናቸውን ነዋሪዎቹ አክለዋል።
በተለይም ምዕራባዊያን አሸባሪውን ጁንታ ለመደገፍ የሚሄዱበት ርቀት ተቀባይነት እንደሌለው ጠቅሰዋል።
ሀገርን ማዳን የህልውና ጉዳይ በመሆኑ ኢትዮጵያዊያን በተባበረ መንፈስ በመስራት ጠላትን ማሳፈር ይኖርባቸዋል ተብሏል።
(በሱራፌል መንግስቴ)