የአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው

የአማራ ክልል ምክር ቤት ጉባዔ

መጋቢት 15/2014 (ዋልታ) የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ።

የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ ለምክር ቤቱ ባሰሙት የመክፈቻ ንግግር አገርን ከብተና ለታደጉና ወራሪው ሽብርተኛ ቡድንን የቀለሰቡ የመከላከያ ሰራዊት፣ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሽ እና ፋኖ ምስጋና አቅርበዋል።

ምክር ቤቱ አንደኛውን መስራች ጉባኤ ካደረገ በኋላ በርካታ ለውጦች ማምጣት መቻሉንም ገልፀዋል።

6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት እየተደረገ ይገኛል።

ምንይሉ ደስይበለው (ከባሕር ዳር)

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW