ሉሲዎቹ ከደቡብ ሱዳን አቻቸው ጋር የአቋም መለኪያ ጨዋታ ሊያደርጉ ነው

ሉሲዎቹ

ሚያዝያ 01/2013 (ዋልታ) – ሉሲዎቹ ከደቡብ ሱዳን አቻቸው ጋር ነገ ምሽት የአቋም መለኪያ ጨዋታ እንደሚያደርጉ ተገለጸ።

ቡድኑ የመጀመሪያውን የአቋም መለኪያ ጨዋታ ነገ ከምሽቱ 12:30 በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚያደርግ ነው የተገለጸው፡፡

ሉሲዎቹ ከመጋቢት 26 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በካፍ የልቀት ማዕከል ቆይታ በማድረግ ልምምዳቸውን እየሰሩ በጥሩ ዝግጅት ላይ ይገኛሉ ነው የተባለው።

የነገውን ጨዋታ ማምሻው ላይ የሚደረገው በአዲስ አበባ ስታዲየም እየተካሄደ በሚገኘው የአገር አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድር ምክንያት መሆኑን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴረሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።