ሉአላዊ ጥቅምን በተመለከተ የሚደረግ ዲፕሎማሲያዊ ጫና የኢትዮጵያን አቋም አያስቀይራትም – አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

ግንቦት 03/2013 (ዋልታ) – በኢትዮጵያ ሉአላዊ ጥቅም ዙሪያ የሚደረግ ዲፕሎማሲያዊ ጫና የኢትዮጵያን አቋም እንደማያስቀይር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አስታወቁ፡፡

በተለያዩ የሀገሪቱ ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች ዙሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥቷል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከአሜሪካው የምስራቅ አፍሪካ ልዩ መልዕክተኛ ፌልት ማን ጋር በሀገሪቱ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል።

(በደምሰው በነበሩ)