ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ኡመር እድሪስ ለኢድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ

ግንቦት 03/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ኡመር እድሪስ ለእስልምና እምነት ተከታዮች ለኢድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ኡመር እድሪስ ባስተላለፉት መልእክት የጾም ፍች ወቅት ዘካተል ፊጥር ከሶላት በፊት መስጠት፣ ተክቢራና ሶላት ማድረስ፣ አቅመ ደካሞችንና ህመምተኞችን መጠየቅ ሃይማኖታዊ ተግባር በመሆኑ መተግበርና 1ሺህ 442 የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም እንዲከበር ህዝቡ የራሱን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።

በዓሉ ሲከበር ሰላማዊ በሆነ መንገድ ሊሆን እደሚገባ የገለፁት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ እድሪስ ሙስሊሙ ህብረተሰብ የሰላም ሰው እንደመሆኑ በዓሉን ሲያከብር የአገሪቱን ሰላም በጠበቀ መልኩ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ እድሪስ አክለውም በዓሉ ሲከበር የጤና ሚኒስቴር ያወጣቸውን መመሪያዎች በጠበቀ መልኩ ሊሆን እንደሚገባም ገልጸዋል።

(በዙፋን አምባቸው)