ሊዮኔል ሜሲ ከሳውዲው ክለብ አልሂላል የዝውውር ጥያቄ ቀረበለት

ሊዮኔል ሜሲ

መጋቢት 26/2015 (ዋልታ) የ35 ዓመቱ የዓለም ዋንጫ አሸናፊው በፒ ኤስ ጂ ያለው ኮንትራት በውድድር ዓመቱ መጨረሻ መጠናቀቁን ተከትሎ ስሙ ከቀድሞው ቡድኑ ባርሰሎና እንዲሁም ከሳውዲው ቡድን አል ሂላል ጋር ሲነሳ ቆይቷል።

ይሁንና በወጣው መረጃ የሰባት ጊዜ ባሎንዶር አሸናፊው ከሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ሂላል ይፋዊ የዝውውር ጥያቄ እንደቀረበለት ተገልጿል።

በዚህም የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ሂላል ለአርጀንቲናው ኮከብ በዓመት 400 ሚሊዮን ዩሮ የሚያስገኝለትን የዝውውር ጥያቄ ማቅረባቸው ይፋ ሆኗል።

ሊዮኔል ሜሲ አሁን በሚጫወትበት ፒ ኤስ ጂ ኮንትራቱን እንዲያራዝም በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢቀርብለትም እስካሁን ውሉን ማደስ አልቻለም።

በሙባረክ ፈንታው