የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ያስመዘገበውን ውጤታማ ጉዞ ተቋማዊ እና ዘላቂ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ

መጋቢት 27/2015 (ዋልታ) በ2014 ዓ.ም ይፋ የተደረገው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በአንድ ዓመት ውስጥ ያስመዘገበውን ውጤታማ ጉዞ ተቋማዊ እና ዘላቂ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ያመጣቸው ለውጦች፣ የንቅናቄው ቀጣይነት ማረጋገጥ እና የአምራች ኢንዱስትሪውን በዘላቂነት መደገፍ ላይ ትኩረቱን ያደረገ መድረክ በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አዘጋጅነት እየተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ የተገኙት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ችግር በዘላቂነት መፍታት የሚቻለው ለአምራች ኢንዱስትሪው ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዚህም ዘርፉ ባለፈው ዓመት ካስመዘገበው የ4.6 በመቶ እድገት በተሻለ ዘንድሮ በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በመደገፍ በ10.6 በመቶ ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

በቀጣይም ያሉ ችግሮችን በመለየት የአምራች ኢንዱስትሪው ለኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግሩ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት ለማስቻል ይሰራል ነው የተባለው፡፡

በሳሙኤል ሓጎስ