ልዑኩ በትግራይ ውቅሮ ከተማ በጦርነቱ ወቅት የተጎዱ ፋብሪካዎችን ጎበኘ

ሚያዚያ 19/2015 (ዋልታ) በብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራው የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ልዑካን ቡድን በትግራይ ክልል ውቅሮ ከተማ በጦርነቱ ወቅት ጉዳት የደረሰባቸውን ፋብሪካዎችን ጎብኝቷል።

በጉብኝቱ የሁሉም ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎችና የመንግሥት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የልዑክ ቡድኑ በጉብኝቱ ሰማያታ የእምነበረድ ፋብሪካ እና ሸባ የቆዳ ፋብሪካን ተመልክተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት ፋብሪካዎቹ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

ፋብሪካዎቹ በጉዳት ምክንያት አገልግሎት መስጠት በማቆማቸው በፋብሪካዎቹ ይሰሩ የነበሩ በርካታ ዜጎች ለችግር መጋለጣቸውም ነው የተገለጸው።

የክልሎች ርዕሳነ መስተዳደሮች በበኩላቸው፣ ተቋማቱን መልሶ ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዙ ተናግረዋል ሲል የዘገበው ኢቢሲ ነው።