አርጀንቲና ከቻይና ለምታስገባቸው ምርቶች በዶላር ሳይሆን በዩዋን ልትከፍል ነው

ሚያዚያ 19/2015 (ዋልታ) አርጀንቲና ከቻይና ለምታስገባቸው ምርቶች በዶላር ሳይሆን በቻይና መገባበያ በዩዋን ልትከፍል መሆኑን የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ሚኒስትር ሰርጂዮ ማሳ ገለጹ፡፡

ውሳኔውም እየቀነሰ የመጣውን የአርጀንቲናን የዶላር ክምችት ለማቃለል ያለመ መሆኑ ተነግሯል፡፡

አርጀንቲና በሚያዝያ ወር ብቻ ወደ 1 ቢሊየን ዶላር ግምት ያላቸው የቻይና ምርቶችን በዩዋን ለመክፈል ያቀደች ሲሆን በቀጣይ በየወሩ ወደ 790 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ግምት ያላቸው ምርቶችን በዩዋን እንደምትከፍልም ተጠቁሟል፡፡

ቻይና ከዶላር ውጭ የንግድ ልውውጥ ሥምምነት ከሩሲያ፣ ፓኪስታን፣ ብራዚል እና ሌሎች በርካታ ሀገራት ጋር ማድረጓ ይታወቃል፡፡