መመሪያን የሚጥስ የአውሮፕላን አብራሪም ሆነ ኦፕሬተር ለሚደርሰው አደጋ ኀላፊነት ይወስዳል ተባለ

ሐምሌ 19/2013(ዋልታ) – ማንኛውም የተቀመጠውን መመሪያ የሚጥስ የአውሮፕላን አብራሪም ሆነ ኦፕሬተር ለሚደርሰው አደጋ ሃላፊነት እንደሚወስድ ተገለጸ፡፡
የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ እንደገለጸው የኢትዮጵያ አቪዬሽን ባለስልጣን ቀደም ሲል ሰኔ 23/2013 ዓ.ም የአየር በረራ መረጃ ማሳወቂያ (NOTAM & AIP SUP) ቁጥር A0166/21 እና AIP SUP A04,2021) ማስተላለፉን ገልጿል፡፡
በመሆኑም በተላለፈው መመሪያ መሠረትም ማንኛውም የአውሮፕላን አብራሪም ሆነ ኦፕሬተር የተቀመጠውን መመሪያ ከጣሰ ለሚደርሰው አደጋ ሃላፊነት እንደሚወስድ ተገልጿል።