የጉጂ ዞን ነዋሪዎች ለመከላከያ ሠራዊት ሰንጋዎች እና ፍየሎችን ድጋፍ አደረጉ

ሐምሌ 19/2013(ዋልታ) – በኦሮሚያ ክልል የጉጂ ዞን ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ከ2 ሚሊዮን በላይ ብር ወጪ የተደረገባቸው 60 ሰንጋዎች እና 80 ፍየሎችን ድጋፍ አድርገዋል።

የመከላከያ ፋይናንስ ሥራ ዘርፍ አመራር ሚኒስትር ደኤታ ወ/ሮ ማርታ ሉዊጂ፣ ሕዝቡ ከመከላከያ ሰራዊታቱ ጎን በመሆን ላደረገው ስጦታ ምስጋና ማቅረባቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።