ሚኒስቴሩ በተለያዩ የማኅበረሰብ አገልግሎት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን በጎ ፈቃደኞች አስመረቀ

ነሐሴ 1/2014 (ዋልታ) የኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስቴር ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በተለያዩ የማኅበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 1 ሺሕ 535 ብሔራዊ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን ለ4ኛ ጊዜ በጅማ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በዛሬው ዕለት አስመርቋል።
ሰልጣኞቹ ለ30 ቀናት በተለያዩ የማኅበረሰብ አገልግሎት ዘርፎች ስልጠና መከታተላቸውም ተገልጿል።
ሚኒስቴሩ ‘በጎነት ለአብሮነት’ በሚል መርህ በጀመረው እንቅስቃሴ የዛሬ ተመራቂዎችን ሳይጨምር በ3 ዙሮች በጅማ ዩኒቨርሲቲ ከ7 ሺሕ 500 በላይ ሰልጣኞችን ማስመረቅ ችሏል።
ከተመራቂዎቹ መካከል አካል ጉዳተኞችና አይነ-ስውራን ወጣቶች ይገኙበታል።
ሳሙኤል ዳኛቸው (ከጅማ)