ሚኒስቴሩ ከምግብ ዘይት አምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር በዘርፉ በሚታዩ ተግዳሮቶች ዙሪያ ምክክር እያካሄደ ነው

ሰኔ 21/2013 (ዋልታ) – የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከምግብ ዘይት አምራች ኢንዱስትሪዎች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት በዘርፉ በሚታዩ ተግዳሮቶች ዙሪያ ምክክር እያካሄደ ነው፡፡

የውይይት መድረኩ አምራቾች የሚያጋጥማቸውን የግብዓት አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ ያለመ ነው ተብሏል፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል የምግብ ዘይት ፍላጎትን ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ምርት ለመሸፈን እንዲሁም ሀገር በቀል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ዘርፉ ለሀገር ኢኮኖሚ የሚያበረክተውን ድርሻ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 232 የምግብ ዘይት አቀነባባሪዎች ስራ ላይ እንደሚገኙና ከነዚህ ውስጥ 26ቱ መካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ሲሆኑ፣ 206ቱ አነስተኛ የምግብ ዘይት አቀነባባሪዎች መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

(በሳሙኤል ሀጎስ)