ሚኒስትሯ በትራንስፖርት ዘርፍ መሪ የልማት ዕቅድ ተግባራዊነት ላይ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

የካቲት 11/2013 (ዋልታ) – የትራንስፖርት  ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ በ10 ዓመታት በሚተገበረው  የትራንስፖርት ዘርፍ መሪ የልማት ዕቅድ ተግባራዊነት ላይ ከአፍሪካ ልማት ባንክ  ዳይሬክተር ጋር ተወያይተዋል።

የኢፌዴሪ የትራንስፖርት  ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ኤክስኪውቲቭ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ።

በተለይም ባንኩ በኢትዮጵያ ለልማት ሥራ ከሚያዉለው 1.65 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዉስጥ 31% በትራንስፖርት ዘርፍ ላይ እንደሚዉል ይታወቃል።

በሌላ በኩል በልማት ባንኩ ድጋፍና ብድር በሚሰሩ  የትራንስፖርት መሰረተ ልማቶች እና ሌሎች ፕሮጀክቶች ተግባራዊነት ላይ በሚታዩ አንዳንድ የአፈፃፀም ችግሮች ዙሪያም ተወያይተዋል።

የልማት ባንኩም የተለመደውን አጋርነት በትራንስፖርት ዘርፉ ላይ አጠናክሮ በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጓል።

ቀጣይ በሚኖሩ የልማት ስራዎች በተለይም ብሔራዊ የትራንስፖርት ፖሊሲን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችለዉን የትራንስፖርት ዘርፍ የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድን ለማሳካት ከባንኩ ጋር በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ከሚንሰትሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡