የፀሀይ ባንክ የምስረታ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

የካቲት 11/2013 (ዋልታ) – ፀሀይ ባንክ የባለ አክሲዮኖች የምስረታ ጉባኤ እያካሄደ ነው፡፡

የባንኩ ምስረታ ዋና አላማ በኢትዮጵያ የፋይናንስ አገግሎት ተደራሽነትን እና  አካታችነትን ያቀፈ ስራን በመስራት የሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ  እድገትና ብልፅግና ለማሻሻል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ባንኩ 740 ሚሊዮን ብር ገደማ ካፒታል እንዲሁም 373 የአክሲዮን ገዢዎች ቁጥር እንዳለውና ባንክ ለመመሥረት የሚያስችል የካፒታል መጠን ያሟላ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በመስራቾች ጠቅላላ ጉባኤም የባንኩ መተዳደሪያና መመስረቻ ደንብ የፀደቀ ሲሆን ባንኩን በቦርድ ዳይሬክተርነት የሚመሩ 12 የዳይሬክተሮች ቦርድ መርጧል::

ለመካከለኛና አነስተኛ የንግድ ስራዎች፣ ለግብርናው ዘርፍ እና ለአምራች ኢንዳስትሪው አስተማማኝ አጋር መሆን የባንኩ ተቀዳሚ መርህ እንደሆነም ተገልጿል::

(በሄብሮን ዋልታው)