ሚኒስትሯ የኢትዮጵያን ነፃነት ለማረጋገጥ የኢኮኖሚ ነፃነት ማረጋገጥ አለብን አሉ

ሙፈሪሃት ካሚል

ግንቦት 15/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያን ቀጣይ ነፃነት ለማረጋገጥ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ነፃነት ማረጋገጥ አለብን ሲሉ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ።

ሚኒስትሯ ይህንን ለማረጋገጥ በሥራ ፈጠራ እና ቴክኖሎጂ ላይ በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

የኦሮሚያ ክልል በሥራ ፈጠራ እና ቴክኖሎጂ ዘርፍ አመርቂ ውጤት ላስመዘገቡ አካላት እውቅና በሰጠበት ሥነ-ሥርዓት ላይ የታደሙት ሚኒስትሯ ሙያን ማክበር እና እውቅና መስጠት የተደበቁ ልዩ ክህሎት ያላቸው ወጣቶችን ለማውጣት ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልጸዋል።

ለሥራ እድል ፈጠራ አና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ክልሉ የሰጠው ትኩረት የሚደነቅ እንደሆነና የፌዴራል መንግሥት ይህንን ጥረት በሁሉም ዘርፍ እንደሚደግፍ ተናግረዋል።

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ላይ የተጀመረው ረፎርም ተጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።

በአሳዬናቸው ክፍሌ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW