ሜሱት ኦዚል ከእግር ኳስ ራሱን አገለለ

ሜሱት ኦዚል

መጋቢት 13/2015 (ዋልታ) የ34 ዓመቱ የአማካይ ስፍራ ተጨዋች ሜሱት ኦዚል ራሱን ከፕሮፌሽናል እግር ኳስ ዓለም ማግለሉን ዛሬ ይፋ አድርጓል።

ሜሱት ኦዚል በተደጋጋሚ ካጋጠሙት ከባድ ጉዳቶች 17 ዓመታትን ካሳለፈበት የሲኒየር ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ህይወት እንዲርቅ እንዳስገደደው ተገልጿል።

ሜሱት ኦዚል ባስተላለፈው መልዕክትም “ከብዙ ማሰብና ማሰላሰል በኋላ ይህንን ውሳኔ ወስኛለሁ፤ ያለፉትን 17 ዓመታት በእግር ኳሱ ዓለም የተሳካ ጊዜያት ማሳለፍ ችያለሁ፤ ነገር ግን አሁን ከእግር ኳስ ዓለም የምሰናበትበት ጊዜ ደረሷል ብሏል፡፡

ኦዚል በእግር ኳስ ዘመኑ የተጫወተባቸው ሪያል ማድሪድ፣ አርሰናል፣ ወርደር ብሬመን፣ ሻልካ፣ ፒነርባቼ እና ኢስታንቡል ባሳሽኬርን አመስግኗል፡፡

ኦዚል በእግር ኳስ ህይወቱ 737 ጨዋታ አድርጎ 262 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ሲያቀብል 137 ግቦችን ደግሞ ከመረብ አሳርፏል።

በሙባረክ ፈንታው