ምርጫ 2013 ቁልፍ የሽግግር ምዕራፍ በሚል በጠ/ሚ ፅህፈት ቤት ውይይት እየተካሄደ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ምርጫ 2013 ቁልፍ የሽግግር ምዕራፍ በሚል ከፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና ከሲቪክ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት እያካሄዱ ነው።

ውይይቱ ዐበይት ባለ ድርሻ አካላት ያላቸውን ሚና እና ኃላፊነት እንዲሁም የምርጫ ስርዓትን በሚያስቃኝ ገለጻ እየተደረገ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

ዐበይት ዴሞክራሲያዊ ተቋማት መሠረታዊ ለውጥ ማካሄዳቸውን ተከትሎ የሚከናወነው ታሪካዊ ምርጫ፣ ከ2010 አንስቶ ኢትዮጵያ በዴሞክራሲ ጎዳና የምታደርገው ጉዞ ዓይነተኛ ማሳያ ይሆናልም ተብሏል።