በሩዋንዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለህዳሴ ግድብ ከ21 ሺህ ዶላር በላይ አበረከቱ

በሩዋንዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለህዳሴ ግድብ በቦንድ ግዥና በድጋፍ 21 ሺህ 300 ዶላር አበረክተዋል፡፡

በሩዋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሉሊት ዘውዴ በሩዋንዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

አምባሳደሯ ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቶቿን ለመጠቀም ያላትን ሕጋዊና ተፈጥሮአዊ መብቶችን በተመለከተ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ መሰራት እንዳለበት መጠቆማቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡