ምክር ቤቱ ለ2014 በጀት ዓመት የ561.7 ቢሊየን ብር ረቂቅ በጀት አፀደቀ

ግንቦት 28/2013 (ዋልታ) -የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ለ2014 በጀት ዓመት የ561 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ረቂቅ በጀት አፅድቋል፡፡

በጀቱ ምርታማነትን ለማሳደግ ትልቅ ትኩረት የሰጠ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገልፀዋል፡፡

ይህም ከ10 ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ ጋር የተጣጣመ እንደሚያደርገው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡